በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሐሚልተን መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን መተዳደሪያ ደንብ መሰረት በሰበካ ጉባኤ አባልነት የሚያገለግሉ አባላት በየሦስት ዓመቱ እንደሚመረጡ ይታወቃል።
በመሆኑም አሁን በሥራ ላይ ያለው ሰበካ ጉባኤ December 31፣ 2022 የሦስት ዓመት የሥራ ዘመኑን ስለሚያጠናቅቅ፤ ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ቤተ ክርስቲያኑን የሚያገለግሉ አባላት ለመምረጥ ይቻል ዘንድ ፦
1. ታህሣስ 2 ቀን 2015 ዓ.ም (December 11,2022) አስመራጭ ኮሚቴ፤
2. ታህሣስ 9 ቀን 2015 ዓ.ም (December 18,2022) የሰበካ ጉባኤ፤ ምርጫ ስለሚካሄድ የቤተ ክርስቲያኑ አባል የሆናችሁ በሙሉ ከላይ በተጠቀሱት ቀናት በቤተ ክርስቲያን ተገኝታችሁ የአስመራጭ ኮሚቴውንም ሆነ የሰበካ ጉባኤውን እንድትመርጡና የቤተ ክርስቲያን አባልነታችሁን ግዴታ እንድትወጡ በቤተ ክርስቲያናችን ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ልዑል እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ካናዳን በሰላም ይጠብቅ::
Comentarios